የገንዘብ ሚኒስተር በበኩሉ በየከተሞቹ የሚገኙ ሁሉንም አካላት በስፋት አወያይተናል ብሏል።
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት አዋጁ ዝቅተኛውን ማህበረስብ ታሳቢ ያደረገ ነው ወይ የሚጨመረው የታክስ ፐርሰንትስ አልተጋነነም ወይ የሃገራችን ህዘብ አይቸገርም ወይ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
አንድን አዋጅ ድንገት አምጥቶ ማጽደቅ ሳይሆን ነገሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ውይይቶች መደረግ አለባቸው ሲሉም ጠይቀዋል፡
አንዳንዱ ነዋሪ አሪፍ ቤት ያለው ይመስላል ግን ኑሮው ቢታይ ግን ከእጅ ወደ አፍ ነው ሲሉም የምክር ቤቱ አባላት እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት የቤት ግብር በአዋጁ 25 በመቶ ነው ሲል ይጠቅሳል ለምን በ5 በመቶ አይሆንም ችግሩ ምንድን ነው እንደሃገራችን መኖር ይባናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አባላቱ ጡረተኞች ጡረታ ሲወጡ ሃብታቸው ቤታቸው ነው ያሉ ሲሆን ድሮ በስራ ሂወቱ ቤት ሲገዛ ከግብር በተረፈው በመሆኑ አሁን ላይ ድጋሚ እንዲቆርጥ መደረጉ አግባብ አደልመ ሲሉ አንስተዋል፡፡
በዚህም ጠረተኞችን መኖሪያ እንዳናሰጣቸው ስጋት እንዳደረባቸውም ምክር ቤቱ አባለት ተናግረዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒሰተር ለምክር ቤቱ አባላት ምላሽ የሰጠ ሲሆን በሁሉም ከተሞች የሚገኙ የህበረተስብ ተወካዮችን በሚገባ አወያየይተን ነው የቀረጽነው ብሏል፡፡
የንበረት ታክስ ግብር ዝቅተኛውን የህበረተሰብ ክፍል በስፋት ያመከለ ነው የሚለው ሚኒስትሩ ግበሩ ብምላሹ ለልማት ነው የሚውለው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ለአለም አሰፋ
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
