“የኛን ምርት ለኛ ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር በፍልውሃ አዲስ አወትሌት ሴንተር በዛሬው እለት ተከፍቷል ።
ይህ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር ከታህሳስ 18 ቀን ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኗል::
እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይም ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ኢንተርፕረይ ልማት ማህበረ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉሴ አለባቸው ፤ይህ ሀገር አቀፍ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር በምርት ትውውቅና ሽያጭ እንዲሁም እርስ በርስ የተሞክሮ ልውውጥና ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ለመስራት የስችላል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ የዘርፉ ልማት እንደ ሀገር ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለማሳየት የሚያስችል መድረክ ነው ያሉት ።
በባዛሩ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 70 የሚሆኑ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ ዉጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች፣ በእንጨትና ብረታ ብረት ዉጤቶች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተገኝተዉበታል ።
ዶ/ር ንጉሴ አለባቸው ፤ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የንግድ ልማት አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ ያሉ ችግሮችና ክፍተቶች መለየታቸውንም ነገረውናል፡፡
በዚህም በጥናቱን መሰረት እንደመነሻ ለተመረጡ 400 ኢንተርፕራይዞች የድጋፍ እና ልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለውናል፡፡
ከዚህ ባለፈ የገጠር ኢንዱስትሪላይዜሽን ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ በገጠር የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም መታቀዱንም ጠቁመዋል ።
ይህም የየአካባቢዉን ሃብትና ጉልበትን መጠቀም ከማስቻሉም በላይ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ፕሮግራሙ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም
