የሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮርዳኖስ ፍቃዱ ፤ለበጎ ስራ ተባበሩ መልካም ማድረግ ለራስ ነው እና” ሲሉ ተናግሯል።
ስራ አስኪያጁ ለተከታታይ ስምንት አመታት በደብረ ብረሃን ከተማ ለ1ሺህ 5 መቶ ለሚሆ የተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ እየሰጡ መሆኑን ነግረውናል።
እንክብካቤና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቆይተው ለዳኑት ተረጂዎች የስራ እድል በመፍጠር፣በመጦር፣ፈጣሪ በሞት የጠራቸውን እንደ እየምነታቸው ቀብር ስነ ስርዓት ሲያስፈፅም መቆየቱን ሰምተናል።
አቶ ዮርዲያኖስ ድርጅቱ በአሁን ስዓት በቋሚነት 250፣በተመላላሽ 150ና ቤት ለቤት 100 በድምሩ 500 ጧሪ፣ቀባሪ፣ ደጋፊ የሌላቸውን አረጋውያን እናትና አባቶቻችንን የአልጋ ቁራኛዎችንና የአዕምሮ ህሙማንን በመያዝ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ሆኖም ግን ድርጅቱ ውስጥ ቋሚ ድጋፍ እና እንክብካቤ የሚሰጥ አካል ውስን በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና በጎ አድራጊ እንዲደግፈን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሀላፊው ድርጅቱ መደገፍ የሚችሉባቸው መንገዶች የዘረዘሩልን ሲሆን በቀን 1 ብር ለ1 ወገን በቋሚነት በመቆጠብ የዓመቱን 365 ብር በመክፈል አባል መሆን ቀዳሚ ነው ብለውናል።
ከዚህ ባለፈ የአንድ ግዜ እና ቋሚ ገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ፣የምግብ ድጋፍ እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ ባቄላ፣በርበሬ፣ዘይት መለገስ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል ።
የአልባሳት ድጋፍ ፦ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ፍራሽ፣ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ምግብ ማብሰያና መመገቢያ ቁሳቁሶች የዳቦ መጋገሪያ ማሽን፣ እንጀራ መጋገሪያ ምጣድ፣የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ሳህን፣እንሻለን ሲሉም ጠቁመዋል።
የንፅህና ቁሳቁስ (ዳይፕር.፣ሞዴስ፣ጓንት፣ፌስ ማስክ፣ላርጎና ሳሙና፣ድጋፍ እንዲደረግላቸው ካነሷቸው መካከል ናቸው።
የደብረ ብረሃን ከተማ አስተዳደር 6ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የሰጠን ቢሆንም ለአረጋዊያኑ መጠለያ ለመገንባት የሚያገለግሉ ቁሳቁስ እንደ ሲሚንቶ፣ ሚስማር፣ አሸዋ፣ጠጠር፣እንጨት፣ወ.ዘ.ተ ድጋፍ እንፈልጋለን ሲሉም ለጣቢያችን ገልፀዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የምንረዳቸው ወገኖች አብዛኛዎቹ በራሳቸው መንቀሳቀስ፣ መመገብና መፀዳዳት የማይችሉ ናቸው እና በፀሎትና በመጎብኘት አስቡንም ብለዋል።
ድርጅቱን ባለቤቶች ለማግኘት በስልክ ቁጥራቸው 09-13-02-34-44 ወይንም 09-82-21-21-21ይቻላል ።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
