በተፈጥሯቸው አስፈላጊ ንጥረ ነገር ያልያዙ ምግቦችን በአስፈላጊው ንጥረ ነገር ማበልጸግ ችግሩን እንደሚቀርፍ የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ መኩሪያ ተናግረዋል።
በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና ሩዝን የማበልጸግ ስራዎች መፍትሄ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
እነዚህን ምግቦች ማበልጸግ ወጪውን ከፍተኛ አያደርገውም የሚሉት አቶ በቀለ፤ አንድ ኪሎ ፉርኖ ዱቄትን ለማበልጸግ 1 ብር ብቻ ተጨማሪ ወጪ እንዳለው አንስተዋል።
በአውሮፓውያኑ 2011 ጨውን የማበልጸግ ስራ መጀመሩን ገልጸው፤ በ2022 አምራቾች ምግቦችን ማበልጸግ እንዳለባቸው ግዴታዎች መቀመጣቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ምግብ ማበልጸግን ዘግይታ መጀመሯን የሚናገሩት ስራ አስኪያጁ፤ የምግብ ማበልጸጊያ ንጥረ ነገሮች ከውጭ የሚመጡ በመሆናቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣው ጥናት፤39 በመቶ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት የቀነጨሩና 22 በመቶው ደግሞ መሆን ካለባቸው ክብደት በታች ናቸው ማለቱ ይታወሳል።
ሊዲያ ደሳለ
ታኀሣሦ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
