ጤና ሚኒስቴር በዛሬ እለት ለወሊድ እና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶችን ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አስረክቧል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አምቡላንሶቹ በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችንን ለማሳካት ሚናቸው የጎላ መሆኑን ስተው ሁሉም የስራ ሀላፊችም እኚህን አምቡላንሶች ለተገቢው አገልግሎት ብቻ እንዲያውሉ አሳስበዋል፡፡
ዶክተር መቅደስ በርክክብ ስነስረአቱ ላይ ባደረጉት አጠር ያለ ንግግር ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ሺህ በላይ አምቡላንሶች ለከተማ አስተዳደሮችና ለክልሎች እንደተላለፉ እና በእናቶች ሞት እና በድንገተኛ አደጋ ቅነሳ ዙሪያ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበም አንስተዋል፡፡
ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
