ዋና ከተማዋን ሪያድን ጨምሮ የደብብ ምእራብ አሴር እና ጃዛን ግዛቶች ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ላይ ወድቀዋል።
ብሄራዊ የሜትሮሎጂ ማእከል በሳዉዲ መካ እና መዲና በሆኑ ቅዱሳን ቦታዎች ላይ ሊደርስ የሚችለዉን የጎርፍ ስጋት ተከትሎ ማስጠንቀቂያዎች እያወጣ ይገኛል።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ዜጎቻቸዉ የጥንቃቄ እና የደህንነት መመሪያዎች እንዲከተሉ እያደረገ ይገኛል።
ፈጣን የአምቡላንስ አገልግሎት እና የነፍስ አድን ቡድኖች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
የከባድ ዝናብ የአየር ሁኔታዉ ለቀናት ይቀጥላል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎች እንዳመላከቱት ከሆነ የጎርፍ መጠኑ እየጨመረ እንደሚገኝ በዚህም መኪናዎች እና ህንፃዎች ጉዳት ያስተናገዱ መሆኑን እያሳዩ ይገኛል።
የአዉሮፕላን በረራዎች በከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት እየተሰሩ እንደሚገኝ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ።
ቁምነገር አየለ
ታኀሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
