በሁሉም የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች የሚመረቁ ቪላዎችን ያካተተዉ ሪዞርት ተመርቋል፡፡

በእያንዳንዱ የአፍሪካ አገራት ቁጥር ቪላዎችን የሰራዉ ኩሪፍቱ አፍሪካን ቪሌጅ ከታህሳስ 26 ጀምሮ ክፍት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የኩሪፍቱ ሪዞርቶች ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸዉ፤ ሪዞርቱ በሸገር ከተማ አስተዳደር የተሰራ ብቸኛዉ ሪዞርት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እያንዳንዱ ክፍል 1መቶ63 ካሬ መሬት ላይ ያረፈ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሪዞርቱ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ሲሰራ መቆየቱን አንስተዉ፤ ለማለቅ ረዘም ያለ ጊዜን የወሰደዉም የድርጅቶቹ መቀያየር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት የሪዞርቱ ስራ በቤተሰብ ቢዝነስ ስር ሆኖ እንዲተዳደር መደረጉን አንስተዉ፤ ለምርቃት መብቃቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ ታዲዮስ ፤ሪዞርቱ 9 የስብሰባ አዳራሾች እና 1ሺህ 2መቶ50 ሰዎችን መያዝ የሚችል የሰርግ አዳራሽ እንዳለዉም ገልጸዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ እና እስከዳር ግርማ

ታኀሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *