በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ እንደሆነ ተነገረ።

ያደረሰው ጉዳት ከ135 ቢሊዮን በላይ እንደሆነም ተገምቷል።

በዚህ ሰደድ እሳት እስካሁን ቢያንስ 10 ሰዎች መሞታቸው ሲነገር ፣ 100,000 የሚጠጉ ቤቶች እና ንግድ ሱቆች መብራት አጥተዋል ተብሏል፡፡

ባለስልጣናቱ ተጨማሪ በአከባቢው ያለው ኃይለኛ ንፋስ እሳቱን የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

አኩዌዘር የተሰኘው ባልደረባ የሆኑ የግል ትንበያ ባለሙያ በሰጡት ቅድመ- ትንበያ መሰረት እሳቱ ያደረሰው ውድመት ከ135-150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ሙያዊ ግምታቸውን ሰጥተዋል።

በአሜሪካ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ ስፍራዎች በእሳት መያያዛቸው ተከትሎ ዋጋውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።

እንደ ሞርኒንግ ስታር እና ጄፒ ሞርኒንግ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ተንታኞች በሰጡት አስተያየት የመድን ኩባንያዎች የሚሰጡት ሽፋን እስከ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣቸው ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።

ፓሊሳዴስ በተሰኘው ሰደድ እሳት ከ5 ሺህ 300 በላይ ህንጻዎች ሲወድሙ በኤቶን እሳት ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ መውደማቸውን የእሳት አደጋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ባለስልጣናቱ አሁንም ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት የጉዳቱ መጠን እየጨመረ መምጣቱ እንደማይቀር ይገመታል።

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *