ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመገናኘት መቸኮላቸዉን ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ ከአምስት ቀን በኋላ ቃለ መኃላ ከፈጸሙ በኋላ ከፑቲን ጋር ቶሎ የመገናነኘት ዕቅድ አለኝ ነዉ ያሉት፡፡
ፑቲን እኔን ለማግኘት ይፈልጋል እኔም ቶሎ ብንገኛን ብዬ አስባለሁ ብለዋል ትራምፕ፡፡
ሁለቱ መሪዎች በአካል ከመገኛነታቸዉ በፊት ከሰሞኑ የስልክ ዉይይት እንደሚደርጉ ይጠበቃል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት ለመቋጨት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡
አባቱ መረቀ
ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
