“ያለአግባብ መሰዋትነት እየከፈልን ያለነው ቁጭ ብለን መወያየት ባለመቻላችን ነው” አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ

ያለአግባብ መሰዋትነት እየከፈልን ያለንነው ቁጭ ብለን መነጋገርና መወያየት ባለመቻላችን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

ሁለተኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ያለአግባብ መሰዋትነት እየከፈልን ያለነው ቁጭ ብለን መነጋገር ባለመቻላችን በመሆኑ መወያየት መነጋገር ብንችል ለችግሮቻችን መፍትሔ መስጠት እንችላለን ብለዋል።

የሀገርን ቀጣይነት በመቻቻል፣ በእኩልነትና ብሄራዊ ጥቅሞችን መሰረት ያደረገ የጋራ ሀገራዊ መግባባት ሊኖር እንደሚገባ ጠቅሰው፣ ባልተግባባንባቸው ጉዳዮች ላይ ሰላማዊ ውይይቶች ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የወደፊቱን በማየትና ከሌሎች በመማር መንጋገር ከቻልን ሀገርን በማልማት ለቀጣዩ ተውልድ ማሸጋገር ይቻላል።

በመድረኩ የብሔራዊ መግባባት ታሪካዊ መሠረቶች በኢትዮጵያ፣ በአሁኗ ኢትዮጵያ የብሔራዊ መግባባት
ተግዳሮቶች፣ የብሔራዊ መግባባት ሚና በቀጣይ ሀገራዊ ግንባታ ላይ ያተኮሩ የመወያያ አጀንዳዎች ቀርበው ምክክር የተደረገባቸው ሲሆን መሰል ምክክሮች በየደረጃው መለመድ አለባቸው ማለታቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል፡፡

ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *