በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኤም 23 አማፅያን መስፋፋት ቀጠናዊ ጦርነት ሊወልድ ተቃርቧል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሓፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኤም 23 አማጽያን መስፋፋት በቀጠናዉ ትልቅ ስጋትን ደቅኗል ብለዋል፡፡

አማፅያኑ በርካታ ግዛቶችን እየተቆጣጠሩ መሆናቸዉን ተከትሎ ቀጠናዊ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸዉን ገልፀዋል፡፡

በርካታ ዜጎች ቤት ንበረታቸዉን ጥለዉ መፈናቀላቸዉንም ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤም 23 አማጽያንን ትደግፋለች በሚል ርዋንዳን እንደሚኮንኑ ይታወቃል፡፡

አሁን ላይ ነገሮች እየከፉ በመሆናቸዉ የቀጠናዉ አገራት የዲሞክራቲክ ኮንጎን ሉዓላዊነት እንዲያስከበር ተመድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *