ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ጀቢና ፊልም ሊመረቅ ነው፡፡

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ጀቢና ፊልም የፊታችን ሰኞ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለዕይታ ይቀርባል።

በደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር /የእማዬ ልጅ / የተሰራው ይህ ፊልም በአንዲት ወጣት ሴት የህይወት ትግል ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው ተብሏል፡፡

ፊልሙ ከዚህ በተጨማሪም ባህላዊ የዳኝነት ስርዓታችንን፤ በተለይም የገዳ ባህላዊ ዳኝነት ስርዓት የሚያሳይ መሆኑን ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተነግሯል፡፡

የፊልሙ ኤክስኪዩቲቨ ፕሮዲውሰር እና የፊልሙ መነሻ የሆነውን መሰሶ የተሰኘው መጽሀፍ ደራሲ ሄለን እሸቱ፤ ብዙዎች ከእኔ ታሪክ ይማሩበታል ብዬ ነው የራሴ ታሪክ የሆነውን ጉዳይ ወደ ፊልም የተቀየረው ብላለች።

በፊልሙ በዋና ተዋናይነት ካሳሁን ፍስሀ ማንዴላ፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ ቤቴልሄም ሸረፈዲን ፣አስራት እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ አመት የፈጀ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ነው የተባለው።

ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *