በአካባቢው በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ 9 ሺህ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸውን የገቢረሱ ዞን አስታወቀ።

በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን በ ስድስት ቀበሌዎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ 9 ሺህ 1 መቶ 6 ሰዎች በላይ መኖረያ ቀያቸውን በመልቀቅ መፈናቀላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዱ አሊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

የስጋት ቀጠና ተብለው ከተለዩ አካባቢዎች ሳይነሱ የቀሩ ዜጎችን በማንሳት ወደ ጊዜያዊ መጠለያዎች የማስፈር ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የፌደራሉ መንግስት ከክልሉ እና ከዞኑ ጋር በጋራ በመሆን በአካባቢው ለተፈናቃዮች በቂ እርዳታ እንዲደርስ ለማድረግ እየሰራ ነው ተብሏል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በአካባቢው ለአንድ ሳምንት ትምህርት ተቋርጦ ነበር ያሉት አስተዳዳሪው፤አሁን ላይ በጊዜያዊ ድንኳኖች ውስጥ የማስተማር ስራው መጀመሩን ነግረውናል።

ተፈናቃዮች የጤና አገልግሎትእያገኙ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ፤የሶላር አልትራሳውንድን ጨምሮ ለህክምና ግብአት የሚሆኑ መሳሪያዎችንም እየቀረበ መሆኑንም አንስተዋል።

አቤል እስጢፋኖስ

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *