የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሀላፊ ወደ ኢትዮጲያ ሊመጡ ነው

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር በየካቲት ወር መጀመሪያ ቀናት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለፀ

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከየካቲት 1 አስከ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በጉብኝታቸው ወቅተ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ የገንዘብ ሚኒስቴር ባጋራው መረጃ ገልጿል።

የውይይታቸው ዋነኛ ጉዳዮችም በኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሳጣቸው ፖሊሲዎች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መሆናቸውን መረጃው አመላክቷል።

በተጨማሪም ዳይሬክተሯ በጉብኝታቸው ወቅት ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ ሁኔታ እና በኢኮኖሚ እድሎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱ የጠቆመው የሚኒስቴሩ መረጃ በሀገሪቱ በማህበራዊ ልማት የተሰሩ ስራዎችን እነደሚጎበኙ አስታውቋል፡፡

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እ.ኤ.አ በ2019 የተቋሙ ሃላፊ ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ በመረጃው ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ገቢን ለማሳደግ በሚል እያከናወነች ያለችው የግብ ማሻሻያ እርመጃዎቿ በታሰበው ልክ እየሄደ ይገኛል ሲል አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ትላንት ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማወደሱን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።

ስራ አስፈጻሚ ቦርዱ ትላንት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 248 ሚሊየን ዶላር ብደር ማጽደቁን፤ ትላንት የተለቀቀውን ጨምሮ አይኤምኤፍ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊየን ዶላር ለኢትዮጵያ በተራዘመ ብድር መስጠቱም በመግለጫው ተካቷል።

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *