አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ‘ጠንከር ያለ ውይይት’ እያደረገች ነው ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

ሞስኮ ከዩክሬን ጋር የምታደርገውን ጦርነት መቆም አለበት ሲሉም አክለዋል ትራምፕ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚነጋገሩ አርብ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ትራምፕ በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች “እኛ እንነጋገራን ፤ ምናልባት ጠቃሚ የሆነ ነገር እናደርጋለን ብዬ አስባለሁ፡፡ ያንን ጦርነት ማቆም እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2022 ላይ ፕሬዝዳንት ቢሆኑ ኖሮ “አሰቃቂው” የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት መቼም አይጀመርም ነበር ሲሉ በደግጋሚ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ “ይህ ትርጉም የለሽ ጦርነት መቆም አለበት” ፡፡ ካሉ በኃላ ጦርነቱን ለማስቆም ምንም አይነት ነገር ማድረግ እችላለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

” ውይይት እያደረግን ነው … እየተነጋገርን ነው” ብለዋል ፕሬዝደንት ትራምፕ፡፡

ትራምፕ ከፑቲን ጋር አስቀድመው ተነጋግረዋል ወይ ተብለው ሲጠየቁ፡ “እንዲህ ማለት አልፈልግም። በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም ከባድ ውይይት እያደረግን ነው። ጦርቱ እንዲቋረጥ ለማድረግ እየሞከርን ነው” ብለዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *