‹‹የሰላም ባለቤት›› በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የወጣቶች ሰላምና ደህንነት ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሀገር በቀል እውቀቶቻችንን በመጠቀም ግጭት በሚፈጠርበት ወቅት እዉቀት በተሞላዉ መንገድ ለመፍታት መሞከር ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ ድሮ እና እንዳለፈበት እውቀት ሳይሆን ለአንድነታችንና ለአብሮነታችን ምን ያህል አስተዋጾ እንዳደረገ መመልከት ያስፈልጋል ነዉ ያሉት፡፡

በተለይ ወጣቶች ለሰላም እና ለአንድነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ኮንፍረንስ፤ ሰላምን ማምጣት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ፣ በተባበሩት መንግስታት የሥነ-ህዝብ ልማት ፈንድ ተወካይ ኮፊ ኮዮሜ፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች እንዲሁም ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣቶች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *