በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ከአርሰናል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አንቶኒ ጎርደን እና ሙርፊ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ኒውካስል ዩናይትድ አርሰናልን በድምር ውጤት 4ለ0 በማሸነፍ ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
በፍፃሜው ኒውካስል ዩናይትድ የሊቨርፑል እና ቶተንሀምን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።
ዛሬ ሁለተኛው የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ምሸት 5:00 ላይ ሊቨርፑል እና ቶተንሀምን ያፋልማል፡፡
ጋዲሳ መገርሳ
ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
