የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሴባስቲን ሌኮርኑ፤ ኪየቭ የአየር ክልሏን ከሩሲያ ለመከላከል የሚረዳትን “ሚራጅ 2000” የተሰኘ ተዋጊ ጄቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩክሬን መላካቸውን አስታውቋል።
“ከእነዚህ አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያው ዛሬ ዩክሬን ገብቷል” ያሉት ሚኒስትሩ በመጠን ምን ያህል እንደ ላኩ ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።
ፈረንሳይ ሚራጅ 2000 ሺህ የተሰኘውን ተዋጊ ጀት ድጋፍ ያደረገችው በቅርቡ ለዩኩሬን አብራሪዎች ስልጠና ከሰጠች ቡኋላ ነው።
ድጋፉ ዩክሬን ከራሺያ የሚወነጨፍባትን የሰማይ ላይ ጥቃትን ለመከላከል ይረዳታልም ተብሏል።
ልኡል ወልዴ
ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
