የስልጣን ሽኩቻ በትግራይ ላለዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ መንስኤ  ሆኖ ቀጥሏል  ተባለ።

ይህን ሲል የከሰሰው በክልሉ  የሚንቀሳቀሰዉ ባይቶና ፓርቲ ነው።

በትግራይ ክልል በሁለቱ የህዉሃት ቡድኖች መካከል ያለዉ የስልጣን ፍላጎት በክልሉ ላለዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ መንስኤ ነዉ ሲል ባይቶና ፓርቲ ገልጿል።

ፓርቲዉ ከጣቢያችን ጋር በነበረዉ ቆይታ እንዳስታወቀዉ  በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች መካከል የሚታየው ውዝግብ ከስልጣን እንጂ ፍጹም ከህዝብ ፍላጎት የመነጨ አይደለም ብሏል ፡፡

የባይቶና ትግራይ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርኸ አሁን እየታዩ ያሉ የፖለቲካ ክፍፍሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት ከ98 በመቶ በላይ ስልጣኑን ለህወሓት በመሰጠቱ የተፈጠረ ነው ብለዋል ፡፡

የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የያዙት አቋም የፖለቲካ ቀዉስን የሚያባበስ ነዉ ሲል ተቃዋሚ ፓርቲዉ ባይቶና አስታዉቋል ፡፡

በአቶ ጌታቸው ረዳ እና በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመሩት የህወሓት ቡድኖች መካከል የተፈጠረው የአስተዳደር እና የስልጣን ውዝግብ ከጦርነት በቅጡ ባላገገመው ክልል ላይ ተጨማሪ ቀውስን እንዳያወልድ ከፍተኛ ስጋት እንደሚጭር ተገልጿል ፡

አቤል እስጢፋኖስ

የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *