ኢትዮ ቴሌኮም 61.9 ቢሊየን ብር ማትረፉን ገለፀ።

ኩባንያው በ6 ወራት ውስጥ 61.9 ቢሊየን ብር ማግኘቱን አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም 61.9 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባቱን የገለፀ ሲሆን፤ 72.6 ሚሊየኑ በውጭ ምንዛሬ የተገኘ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ የደንበኞች ቁጥር 80.5 ሚሊየን መድረሱንም የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።

የቴሌብር ደንበኞች ቁጥር 51.5 ሚሊየን መድረሱን የሚያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፤ 5 ሚሊየኑ በ6 ወራት ውስጥ የተገኙ መሆናቸውን አንስተዋል።

ቴሌብር ስራ ከጀመረበት 3 ዓመት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 3.58 ትሪሊየን ብር ግብይት ተፈፅሞበታል ነው ያሉት።

በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ደግሞ 1 ትሪሊየን ብር ግብይት እንደተፈፀመም ገልጸዋል።

በ6 ወራቱ በቴሌብር በተደረገ ግብይት 5.2 ሚሊየኑ በውጭ ምንዛሪ የገባ መሆኑም ተገልጿል።

ለ 3 ዓመት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የሊድ ስትራቴጂ ዕቅድ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *