እስራኤል ሃማስ እስከ ቅዳሜ ታጋቾችን ካልፈታ የጋዛ የተኩስ አቁም ያበቃለታል አለች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃማስ “እስከ ቅዳሜ እኩለ ቀን ታጋቾቻችንን ካልመለሰ” ከባድ ውጊያ እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዋል።

ቤንጃሚን ኔታንያሁ የታጋቾች መለቀቅ ጊዜው መራዘሙን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ እና በአካባቢው እንዲሰማራ ማዘዛቸውን ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በመጪው ቅዳሜ ሶስት ታጋቾች ይለቀቃሉ የተባለ ቢሆንም ኔታንያሁ እየጠየቁ ያሉት ሶስቱን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ቀሪዎቹን 76ቱን መሆኑን አንድ ሚኒስትር ተናግረዋል።

ሐማስ ለሶስት ሳምንታት የሚፈጀውን የመጀመሪያውን የተኩስ አቁም ስምምነት ምዕራፍ “በማወሳሰብ፣ ወይም በማዘግየት እስራኤል ተጠያቂ ናት” ብሏል፡፡

እስካሁን ድረስ ሐማስ 16 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ በእስር ቤቷ የነበሩ 566 ፍልስጤማውያንን ለቃለች።

ለሶስት ሳምንታት በሚቆየው የመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም 33 እስራኤላውያን ታጋቾች እንዲሁም 1 ሺህ 900 ፍልስጤማውያን ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስራኤል ከ33ቱ ውስጥ ስምንቱ መሞታቸውን አስታውቃለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *