ሃማስ ከእስራኤል እና ከዩኤስ ለሚሰነዘሩ ዛቻዎች እንደማይንበረከክ አስታወቀ፡፡

የፍልስጤም ቡድን ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ፤ ፍልስጤማውያንን ከ ጋዛ ምድር ለማስጣት የነደፈችውን እቅድ በፍፁም እንደማይቀበል እና ለዚህም እንደማይንበረከክ አስታውቋል፡፡

ትራምፕ በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን በግዳጅ እንዲቀበሉ ዮርዳኖስ እና ግብፅ ላይ ግፊት እንደሚያደርጉ በድጋሚ ቃል ገብተዋል ነገር ግን ሁለቱም አገሮች እስካሁን ይህንን የትራምፕን ሀሳብ ሊቀበሉ አልቻሉም፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ እና የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ በስልክ መነጋገራቸው የተነገረ ሲሆን የፍልስጤም ህዝብ ከመሬታቸው ሳይነሱ የጋዛ መልሶ ግንባታ በአስቸኳይ መጀመር እንዳለበት መስማማታቸውን አሳውቀዋል፡፡

መሪዎቹ የፍልስጤምን ነጻ የሆነች ሀገር በመመስረት በቀጠናው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከትራምፕ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል ብሏል መግለጫው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሃማስ ቡድን ሉኡኩን ይዞ ወደ ግብፅ ማቅናቱ ተሰምቷል፡፡

አልጀዚራ

የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *