በአማራ ክልል ከ4ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው ተባለ

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4 ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በክልሉ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ላይ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

ማክሰኞ የካቲት 4 2017 ዓ.ም በተጀመረው ጉባኤ ርእሰ መሥተዳድሩ በማብራሪያቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከከል የትምህርት ዘርፉ አንዱ ሲሆን በተያዘው በጀት አመት ባለፉት ስድስት ወራት ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሀነዋል ብለዋል።

መምህራንም በታጠቁ ኀይሎች ወከባ እየደረሰባቸው ነው፤ የዚህን ድርጊት ቀጣይ ተጽዕኖ አርቆ በመመልከት የትምህርት ሥራን በጋራ መታደግ ግድ ይላል ብለዋል፡፡

በክልሉ 1ሺ983 ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ ያሉ ሲሆን ክእነዚህ ውስጥ 7ሺ4መቶ44 ወይም 67.77 በመቶ ብቻ ናቸው መደበኛ የትምህርት ስራ ላይ የሚገኙት ተብሏል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *