በ1መቶ 52 አገልግሎቶች ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አለማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም ገለፀ።

ለደንበኞቹ ከሚያቀርባቸው 3መቶ54 አገልግሎቶች ውስጥ 1መቶ52 በሚሆኑት ላይ ምንም አይነት ጭማሪ አለመደረጉን አስታውቋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በአገልግሎቶቹ ላይ ጭማሪ ያደረገው ኩባንያው ፤ በ2መቶ2 አገልግሎቶቹ ላይ ብቻ የዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን ነው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ የገለፁት።

በ6 ወራት ውስጥ የተለያዩ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተደርገው ነበር ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፤ የደረሰብን ጥቃት ግን አልነበረም ብለዋል።

በ6 ወራት ጊዜ ለፋይዳ መታወቂያ 4.2 ዜጎችን ምዝገባ ማድረግ ተችሏል ያሉ ሲሆን፤ 2መቶ56 ሺህ መታወቂያዎችን ማተሙንም ነው የገለፁት።

ለ 3 ዓመት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የሊድ ስትራቴጂ ዕቅድ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *