ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል” ሲል ተናግሯል።
ትላንት ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ በተጨማሪም የስንዴ ምርቷ ስላደገ “ስንዴ ከውጭ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቷል” ብሏል።።
ጽሕፈት ቤቱ በምግብ ራስን መቻልን አስመልክቶ ባወጣው ዝርዝር መረጃ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የውጭ ሀገር የስንዴ ምርት ታስገባ ነበር።
መግለጫው አያይዞም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022/23 የምርት ዘመን ኢትዮጵያ 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ የስንዴ ምርቱ መጠን በቀጠለው ዓመት ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን አውስቷል።
አያይዞም ሀገሪቱ በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏ ስንዴ ከውጭ መግባቱ ይቆማል ማለት ግን እንዳልሆነ ያሳሰበው መግለጫው በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት አሁንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።
የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
