የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ደ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ስራ ይጀምራል ብለዋል።
የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳንና ብሩንዲ መፈረማቸው ይታወሳል።
በስምምነት ማዕቀፉ እንደሰፈረው ከተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስድስት አገራት በፓርላማቸው አጸድቀው ለአፍሪካ ህብረት ካስገቡ የናይል ተፋሰስ ኮሚሽንን ማቋቋም ይቻላል።
እስካሁን ድረስ አራት ሀገራት ስምምነቱን አልተቀበሉትም ያሉት ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን፣ ሁጋንዳና ሩዋንዳ አንድ ላይ በመሆን ፊሪማቸውን ያላሰፈሩትን ኬንያን፣ሱዳን፣ድሞክራቲክ ረፐብሊክ ኮንግ እና ግብፅን የማነጋገር ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
እነዚህን ሀገራት ለማነጋገር የዘጠኝ ወር የጊዜ ገደብ የተሰጠ ሲሆን፤ ከዘጠኙ አራት ወር አልፏል አምስት ወር ይቀራል ሲሉ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
ኬኒያና ዲ.አር.ሲ(DRC) በቅርቡ ይመጣሉ ብለን እናምናለን ነው ያሉት።
“የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ተግባራዊ መሆኑን፤ በስምምነት ማዕቀፉ ውስጥ መርሆዎች፣ መብቶች እና ግዴታዎች ተፈጻሚነትን የሚያመቻች ተቋም እንዲኖር የስችልል ብለዋል።
የስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ በአገራቱ መካከል አለመግባባት ሲከሰትም የሚፈታው በዚሁ ኮሚሽን አማካኝነት ነው።
ሌላኛዉ የዚህ የኮሚሽኑ መቋቋም የተፋሰሱ ሀገራት የልማት ትብብር በህግና ስርዓት እንዲመራ ከማድረጉ በተጨማሪ ለጋራ ጥቅም የሚውሉ ተጨማሪ ግድቦችን ለመስራት እድል እንደሚከፍት ገልጸዋል፡፡
ኮምሽኑን ለማቋቋም የሚያስፈልጉ አባላት እና አስፈለጊ የሆኑ የህግ ማእቀፍ መዘጋጀቱን የጠቀሱት ሚኒስተሩ ከመነጣል በሚል የጊዜ ገደብ ያስቀመጥነው ሲሉ ነግረውናል፡፡
ልኡል ወልዴየናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን በአንድ አመት ውስጥ ስራ ይጀምራል ተባለ ።

ልኡል ወልዴ