አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን(ማርች 8) ምክንያት በማድረግ “እችላለሁ” በሚል መሪ ቃል ለ4ተኛ ጊዜ የሴቶች የተሰጥኦ እና የስራ ፈጠራ ውድድር መጀመሩን ባንኩ አስታውቋል ።
ውድድሩ ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 8 እንደሚቆይ ተነግሯል።
መርሐ ግብሩ በሙዚቃ (በድምጽ)፣ በቲክቶክ ቪዲዮ እና በሥራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተሰጥዖ ያላቸው ሴቶች እንዲሳተፉ የሚጋብዝ መሆኑን ሰምተናል።
በሙዚቃ (በድምጽ) እና በአጭር የቲክቶክ ቪዲዮ አሸናፊ ሆነው ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ እንስቶች ከብር 50,000 – 100,000 የሚደርስ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተነግሯል።
እንዲሁም በሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ 50 ሴቶች ለሥራ ማስፋፊያ የሚሆን በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለመያዣ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት እንደሚዘጋጅላቸው ተጠቅሷል።
ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ሥራ በባለሙያና በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የሕዝብ ድምጽ ተለይቶ አሸናፊዎች የሚለዩ መሆኑ ተነስቷል።
ለመወዳደሪያ የሚቀርቡ ነገሮች ይዘታቸው ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ተብሏል።
በሥራ ፈጠራ፣ በድምፅ እንዲሁም በቲክ ቶክ አጭር ቪዲዮ ተሰጥዖ ያላቸውን እንስቶች አወዳድሮ የሚሸልም መሆኑ ሴቶች ያላቸውን ተሰጥዖ እንዲያጎለብቱና ለሕዝብ በተሻለ እንዲደርሱ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
ሐመረ ፍሬው
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
