ባለፉት ስድስት ወራት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ መታደግ መቻሉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል ።
የአዲስ አበባ እሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሐመድ በከተማው በስድስት ወራት ውስጥ 244 አደጋዎች መከሰታቸውን ነግረውናል።
አብዛኛው አደጋዎች ከጥንቃቄ ጉድለት የተከሰቱ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ኮማንደር አህመዲን አሁን ያለንበት ወቅት እንኳን ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ይቅሩና አፈር የሚነድበት ነው ብለዋል።
ይሁን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዎችን መጠቀማችን በንድሮ አመት እስካሁን ባለው ጊዜ ከተከሰቱ 244 አደጋዎች የሰው ህይወትን ጨምሮ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ መታደግ መቻላቸውን ገልፀዋል።
ተቋሙ የሰዉ ሃይል ከማብቃትና ቴክኖሎጂን ከመላበስ ረገድ የተሰሩ በርካታ ስራዎች አሉ ያሉ ሲሆን በቂ ነው ማለት ግን አይቻለም ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ በተለይም ከአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከሚዲያ ባለሙያዎች ውይይት እያደረገ ይገኛል።
ልኡል ወልዴ
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
