በጀርመን በተቀሰቀሰ የስራ ማቆም አድማ በርካታ የበረራ ጉዞዎች ተሰርዘዋል ተባለ፡፡

በመላው ጀርመን በተቀሰቀሰ የስራ ማቆም አድማ የሙኒክና ፍራንክፈርት ኤርፖርችን ጨምሮ በአስራ ሶስት አየር መንገዶች በረራዎች መሰረዛቸው ተገልጿል፡፡

የሰራተኛ ማህበሩ አድማውን የጠራው ደሞዝን በተመለከተ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

መላው የኤርፖርቶቹ ሰራተኞች አድማ በመምታታቸው በረራዎችን መሰረዝ ግድ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የሰራተኛ ማህበሩ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚጠጉ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ የደሞዝ ስምምነት ላይ መድረስ ይፈልጋል ተብሏል፡፡

የሰራተኛ ማህበሩ ስምንት በመቶ የደሞዝ ጭማሬና ተጨማሪ ጉርሻን በተመለከተ እንዲሁም ሶስት የዕረፍት ቀናት መሰጠት አለባቸው በሚል የቀረበውን የሰራተኛ ማህበሩን እቅድ የፌደራል መንግስቱ አዋጭ አይደለም በማለት ጥያቄውን ዉድቅ እንዳደረገዉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በፊትም ተደርጎ የነበረው ተመሳሳይ የደሞዝ ድርድር እንደከሸፈም ስካይ ኒዉስ አስታዉሷል፡፡

በጀርመን ኤርፖርቶች ላይ የተደረገው የሰራተኞቹ የስራ ማቆም አድማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጓዦችን በረራ እንዳስተጓጎለም ተገልጿል ሲል ስካይ ኒዉስ አስነብቧል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *