የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ በመጋቢት ወር  ከ10 ሺ ዩኒት ደም በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለፀ።

የፆም ወቅት መሆኑን ተከትሎ የደም ዕጥረት መከሰቱንም ሰምተናል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ አለማየሁ  ታረቀኝ፤ መጋቢት የፃም ወቅት መሆኑን ተከትሎ የደም ዕጥረት ሊከሰት መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም ምክንያት መጋቢት ወርን የደም መለገስ ወር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ከበጎ ፈቃደኞች ከሚሰበሰበው የደም አቅርቦት አንጻር እጥረት የሚስተዋልበት ሁኔታ ስለመኖሩ አንስተዋል።

የደም እጥረቱ ከፍ እንዳይል የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የደም ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች፣ በእምነት ተቋማት እና በአውራ ገዳናዎች ላይ ድንኳኖችን በመዘርጋት የደም ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የጾም ወቅት መሆኑን ተከትሎም ምሽት ላይ እና በማይጾምበት ቀን የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *