ለ 1ሺህ ሰዎች ነጻ የኩላሊት ምርመራ ሊደረግ ነዉ፡፡

የዓለም የኩላሊት ቀን በኢትዮጵያ በነገዉ ዕለት ይከበራል፡፡

የኢትዮጵያ ኩላሊት ህመም ማህበር ‹‹የኩላሊት ጤና ለሁሉም›› በሚል መሪ ቃል በብሄራዊ ቲያትር የአለም የኩላሊት ቀንን እንደሚያከብር አስታዉቋል፡፡

እስካሁን 5መቶ እና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ነፃ ምርመራ አድርገናል ያሉት የማህበሩ የቦርድ አባል ዶክተር ቢንያም ግርማ፤ በአሁኑ እስከ 1ሺህ ለሚሆኑ ግለሰቦች የሚሆን ነፃ ምርመራን ማሰባቸውን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም ነፃ ምርመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የአለም የኩላሊት ቀን በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ በየአመቱ በሀገራችን በመጋቢት ወር ይከበራል፡፡

በነገው ዕለት የሚከበረው የአለም የኩላሊት ቀን የተለያዩ ክንውኖች እንዳሉት ገልፀው ነፃ የኩላሊት፣ የደም ግፊት፣ እንዲሁም የስኳር ምርመራን ጨምሮ የባለሙያ ምክርም እንደሚሰጥበት ተናግረዋል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *