“90 በመቶ ህዝብ ሰላምን ስለሚፈልግ ይደግፈኛል” ብለዋል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፡፡
አቶ ጌታቸው ደጋፊዎችን በተመለከተ ወጣቱ ሰላምን ስለሚፈልግ 90በመቶ ህዝብ እኔን እና መስተዳድሬን ይፈልጋል ብለዋል፡፡
90 በመቶ ህዝበ ሰላምን መረጋጋትን የተፈናቃይን መመለስ ስለሚፈልግ ይደግፈኛል ብለዋል፡፡
70 በመቶ ህዝብ ወጣት ነው ስንል ሽማግሌ አይደግፍም ማለት አደልም ሰላም ወዳድ ሁሉ ግን ጊዜዓዊ አስተደዳደሩን ይደግፈዋል ብለዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል መረጋጋት ይፈልገል እንዲሁም ሰላምን ይፈልጋል የጥይት ድምጽ መስማት አይፈልግም ፡፡ለወጣቱም መልክት የሚሆነው ለሰላም ዘብ መሆንን ነው ብለዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
