በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ

ሪያል ማድሪድ፣ አርሰናል፣ አስቶን እና ቦርስያ ዶርትመንድ  ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ
አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ  አትሌቲኮ ማድሪድ በጋላገር ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችሎ ነበር።

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታውን በድምር ውጤት አቻ መሆናቸውን ተከትሎ በተሰጠ መለያ ምት ሪያል ማድሪድ 4ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

አርሰናል ከፒኤስቪ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የመድፈኞቹን ግቦች ዚንቼንኮ እና ዴክላን ራይስ ሲያስቆጥሩ ፔርሲች እና ድርዮች ፒኤስቪን አቻ አድርገዋል።

አርሰናል ፒኤስቪን በድምር ውጤት 9ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

አስቶን ቪላ ከክለብ ብሩጅ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 ያሸነፈ ሲሆን በድምር ውጤት 6ለ1 አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜው አልፏል።

ቦርስያ ዶርትመንድ ከሊል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

የዶርትመንድን የማሸነፊያ ግቦች ኤምሪ ቻን እና ማክሲሚላን ቤር ሲያስቆጥሩ የሊልን ግብ ጆናታን ዴቪድ ከመረብ አሳርፏል።

ቦርስያ ዶርትመንድ ጨዋታውን በድምር ውጤት 3ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች 

ባየር ሙኒክ ከ ኢንተር ሚላን

ባርሴሎና ከ ቦርስያ ዶርትመንድ
 
ፒኤስጂ ከ አስቶን ቪላ

  አርሰናል ከ ሪያል ማድሪድ

የሩብ ፍፃሜ  የመጀመሪያዎቹ  ጨዋታዎች ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም እንዲሁም  የመልስ ጨዋታዎች ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

ጋዲሳ መገርሳ

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *