ባለው የፀጥታ ሁኔታ አማራ ክልል የኤች አይ ቪ ስርጭት ሊባባስ ይችላል ተባለ።

የኤች አይ ቪ መድኃኒት አቅርቦት እና ስርጭት ከፍተኛ ችግር እንደሆነበትም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው በክልሉ ጤና ቢሮ የቲቢ ፣ስጋ ደዌና ኤች/አይቪ ኤድስ መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ ገብሬ ንጉሴ፤ ጥናት ባይደረግም ባለው የፀጥታ ሁኔታ የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍ በማለቱ ስርጭቱ ሊጨምር እንደሚችል ስጋት መኖሩን ነግረውናል።

በተረጋጋ ሁኔታ የጤና ትምህርት ለመስጠት ባለመቻሉ፣

በተፈናቃይ ካምፖች ያሉ ነዋሪዎች ቁጥር መጨመር፣ ብዙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው ችግሩን እንደሚያባብሰው ነው የገለፁት።

በክልሉ የኤችአይቪ መድኃኒት ዕጥረት መኖሩን ያነሱት ዳይሬክተሩ ፤ ችግሩ አሁንም መቀጠሉን ተናግረዋል።

ካለው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ከዋናው ማዕከል መድኃኒቶች በካርጎ ጭምር የሚላኩ ቢሆንም፤ ዋጋቸው ውድ ከመሆኑ በላይ የሚፈያስፈልጉ መድኃኒቶች እየመጡ እንዳልሆነ ነው የገለፁት።

አሁንም ድረስ አስቸጋሪ የሆነብን ከክልል ወደ ጤና ተቋማት መድኃኒቶችን ማከፋፈል ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተቻለን መጠን አገልግሎት ብንሰጥም የግብአት ዕጥረቱ ሊፈታ አልቻለም ብለዋል።

በክልሉ በ6 ወራት ከ1መቶ 58 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኤችአይቪ ታማሚዎች ህክምና ማግኘታቸውንም ዳይሬክተሩ ነግረውናል።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *