የገንዘብ ግምታቸው 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት ተፈጽሞብኛል አለ ኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በ2017 ዓ.ም ሰባት ወራት ውስጥ የገንዘብ ግምታቸው 50 ሚሊዮን 222 ሺህ 9 መቶ 87 ነጥብ 7 ብር የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም ላይ ተፈፅሟል ተባለ፡፡

በአጠቃላይ 163 ወንጀሎች ተፈጽመው ክትትል እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተቋሙ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተፈፀመው ስርቆትና ውድመት የኃይል ሰርቆት፣ የትራንስፎርመር ስርቆት፣ ቆጣሪ መነካካት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት፣ የመሰረተ ልማት ሰርቆት፣ የተቋሙ ሰራተኞችን ስራ እንዳይሰሩ ማወክ እና የኬብል ሰርቆትን የሚያጠቃልል ነው፡፡

በጊቤ 3 ኃይል ማመንጫ 66 ኪ.ቮ ታወር ላይ በተፈጸመ ስርቆት ምክንያት በግድቡ አካባቢ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ኃይል አቅርቦት መቋረጡንም ነግረውናል፡፡

እንዲሁም በፍኖተ ሰላም 66 ኬቪ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት የለም ብለዋል፡፡

በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችም ችግሩ ተፈቶ ወደ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የሚል መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *