ኬኒያ ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ድጋፍ ሰጪ ታጣቂ ቡድንና አጋሮች ስብሰባ አመቻችታለች በማለት ማዕቀቡን መጣሏን ሱዳን አስታዉቃለች፡፡
የሱዳን ካቢኔ ውሳኔን መሰረት በማድረግ በባህርም ሆነ በየብስ እንዲሁም በአየር የኬኒያ ምርቶች ወደ ሃገሪቱ እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንደምታደርግ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
የሱዳን የንግድና አቅርቦት ሚኒስቴር፤ ዉሳኔዉ የሱዳንን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ ብለዉታል፡፡
ኬኒያ በሱዳን ስለተጣለባት የምርቶች እገዳ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡
ኬኒያ ከሱዳን መንግስት ጋር እየተዋጋ ለሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ሃይል የተለያዩ ድጋፎችን ታደርጋለች በሚል በሱዳን ተደጋጋሚ ክሶች ይቀርቡባታል ሲል ሱዳን ትሪቡን አስነብቧል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
