በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሪያል ሶሴዳድን 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለቀያዮቹ ሴጣኖች የማሸነፊያ ግቦችን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሶሰት እና ዳሎት ከመረብ ሲያሳርፍ ለሪያል ሶሴዳድ ኦያርዛባል አስቆጥሯል።
ማንችስተር ዩናይትድ ሪያል ሶሴዳድን በድምር ውጤት 5ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል። በሩብ ፍፃሜው ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኦሎምፒክ ሊዮን ጋር ይገናኛል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በአውሮፓ መድረክ ከማርከስ ራሽፎርድ በ2020 አርቢ ላይፕዚሽ ላይ ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ለማንችስተር ዩናይትድ ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ አስር የፍፁም ቅጣት ምቶችን በማስቆጠር በዩሮፓ ሊግ ታሪክ በርካታ ፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ተጨዋች ሆኗል።
ቶተንሀም ከ አልካማር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።
የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦችን ኦዶበርት ሁለት እና ጀምሰ ማዲሰን አስቆጥሯል።
ቶተንሀም በቀጣይ ከ ፍራንክፈርት ጋር ይገናኛል።
በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ቼልሲ ኮቤንሀቨንን በዲውስቡሪ ሀል ግብ 1ለ0 አሸንፏል።
ቼልሲ ውጤት 3ለ1 አሸንፈው ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል። ቼልሲ በሩብ ፍፃሜው ከ ሌግያ ዋርሳው ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
መመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
