የዲሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትግል ለማገዝ ወደ ሃገሪቱ ገብተው የነበሩ ወታደሮች ለቀዉ እየወጡ መሆናቸዉ ተሰምቷል፡፡
የማሊና ደቡብ አፍሪካ መንግስታት ከሁለት አመት በፊት የኮንጎን ጦር ለማገዝ ወታደሮቻቸውን ልከው የነበረ ሲሆን፤ በኤም 23 ታጣቂ ቡድን ህይወታቸው ያለፈ ወታደሮቻቸው ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ሃይላቸዉን ለማስወጣት መገደዳቸው ተገልጿል፡፡
ከደቡብ አፍሪካ፣ ከማሊና ታንዛኒያ በአጠቃላይ አስራ ዘጠኝ ወታደሮች በታጣቂ ቡድኑ መሞታቸው ተነግሯል፡፡
ኤም 23 የተሰኘው ታጣቂ ቡድን በዋናነት በሩዋንዳ የሚደገፍ ሲሆን፤ በዚህ ዓመትም በኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኙትን ሰፋፊ የማዕድናት ቦታዎች መቆጣጠሩ ተሰምቷል፡፡
የኮንጎ ጦር ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በሚያደርገው ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
ኤም 23 ታጣቂ ቡድን ባለፈው ወር መጨረሻ በግዝፈቷ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትቀመጠዉን ቡካቩ ከተማን መቆጣጠሩ ተነግሯል ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ ፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
