ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሆኘ ኦክስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ክሊኒካል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ፋሲካ በቀለ፤በህይወት ከሚወለዱ 8መቶ ህፃናት ቢያንስ አንድ ህፃን ከዚህ ችግር ጋር እንደሚወለድ ነግረውናል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በየአመቱ ከ1 መቶ ሰባ ሺ በላይ ህፃናት ከዚህ ችግር ጋር እንደሚፈጠሩ ተናግረዋል።
በዋነኝነት ይህ ችግር ህፃናትን ከዉልደት ጊዜ ጀምሮ እንደሚያጠቃ ያነሱት ባለሙያዉ፤በተደጋጋሚ ጥናቶች ቢደረጉም ምክንያቱ ሊታወቅ አለመቻሉን ገልፀዋል።
ችግሩ በዓለም ደረጃ እንዲሁም በአገራችን ዉጤታማ የሆነ የህክምና አማራጭ እንዳለዉ ተናግረዋል።
ይሄ ችግር በማንኛዉም በሚወለዱ ህፃናት ላይ ስለሚከሰት ህብረተሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን አመለካከት መቀየር እንዳለበት ተናግረዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም
