የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን በምትገኘው ሆሳዕና ከተማ ወደ ተለያዩ ሀገራት ድንበር ለመሻገር ከሰባት መቶ ሺህ ብር እስከ አንድ ሚሊየን ብር እየተጠየቀ እንዳለ ሰምተናል።
በዛ ያለ ቁጥር ያላቸዉ ወጣቶች ከአካባቢያቸው መልቀቅን እያዘወተሩ እንደሚገኝ እና ከቦታዉ የመሸሽ ሁኔታ ስለመስተዋሉ ተገልፆል።
ለዚህም ሰፊ የስራ እድል አለመመቻቸት በዋነኝነት ቢጠቀስም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር መፍለስን በአካባቢው ባህል እየሆነ መምጣቱን ሰምተናል።
በዚህም ጉዞ ቤተሰቡ ሆነ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች የሚሳተፉበት እየሆነ መምጣቱም እየተገለፀ ነዉ።
ጉዳዩ ወንጀል መሆኑን ካለመረዳት የተነሳም ሰዎች በማዘዋወር ድርጊት ያሉ ደላሎች የህግ ሂደት በሽምግልና እንዲያልቅ እየተደረገ መሆን ችግሩን እያሰፋዉ ነዉ ተብሏል።
በሆሳዕና ከተማ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ጭማሪ እየታየ መሆን እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የመሬት እጥረት መግጠሙን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በየካቲት ወር የኢትዮጵያ ሰላም ምርምር ተቋም የወጣዉ ሪፖርት በሆሳዕና ከተማ ጫፎች መደበኛ ያልሆነ የመሬት ገበያ መፈጠሩን በዚህም አርሶ አደሮች መሬታቸዉን ከደቡብ አፍሪካ ለሚመለሱ ዲያስፖራዎች እየሸጡ እንደሚገኝ ለማወቅ ችሏል።
ሆሳዕና ከተማ ወደ ደብብ አፍሪካ ፍልሰት በማድረግ ባሉ ዜጎች አዳዲስ ለዉጦች እያሳየች ነዉ ቢባልም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እየተደረጉ ያሉ ጉዞዎች አሳሳቢ እየሆኑ ነዉ ተብሏል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
