በተያዘው በጀት ዓመት ሀገሪቱ የ8.4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝብ እየሰራች መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፡፡

በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች ሲሉም ገልጸዋል።

በኢኮኖሚ ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡም ፤ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ በመዘጋጀት እየሰራች እንደምትገኝ አንስተዋል፡፡

የ10 ዓመቱን መሪ ዕቅድ መነሻ ያደረገ የ5 ዓመት እና የ1 ዓመት የተግባር ዕቅድ ተዘጋጅቶ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም ሀገሪቱ የ8.4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝብ እየሰራች መሆኗን ገልጸው ፤ ባለፉት 8 ወራት የተደገውን አበረታች ጥረት ማስቀጠል ከተቻለ ዕቅዱን ማሳካት እንደሚቻል አመላክተዋል በማብራሪያቸው፡፡

ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ቢያጋጥሙም ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፡፡

ለዓለም አሰፋ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *