አዲስ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በቀጣዩ አመት ይከፈታል ተባለ፡፡

የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በሚቀጥለዉ ዓመት በኢትዮጵያ እንደሚከፈት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የማዳበሪያ ፋብሪካ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ይከፈታል ብለዋል፡፡

ከግሉ ዘርፍ ጋር መክፈት ካልተቻለ መንግስት ብቻውን ይህን በሚቀጥለዉ ዓመት እዉን ያደርገዋል ሲሉ ለምክርቤቱ አባላት አስታዉቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት በገፍ በየዓመቱ ከዉጭ ከምታስገባቸዉ መካከል የአፈር ማዳበሪያ አንዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጲያ በቀን 150 ሺ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ታስገባለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 24 ሚለየን ኩታል ገደማ የአፈር ማደበሪያ እንደ ሀገር ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

ይህ ብቻም አይደለም ለእያንዳንዱ አርሶ አደር በወታደር አጅበን እናደርሳለን ፤ ታዲያ ይህ ሁሉ ችግር የሚፈታው የማዳበሪያ ፋብሪካ ሲፈከት ነው ብለዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *