ሸገር ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ!

የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

በከፍተኛ ሊጉ የምድብ ‘ሀ ‘ በሀዋሳ ከተማ ውድድሩን እያደረገ የሚገኘው የአሰልጣኝ በሽር አብደላ ሸገር ከተማ ዛሬ ከ5:00 ጀምሮ እንጅባራ ከተማን በገጠመበት ጨዋታ 5 ለ 1 አሸንፏል።

የሸገር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች  ሄኖክ አየለ፣ አቤነዘር ሆቴ፣  መስዑድ ታምሩ ፣ ምስጋና ሚኤሳ ፣  ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመራው ሸገር ከተማ ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን 45 በማድረስ  ከተከታዩ ቤንች ማጂ ቡና በ13 ነጥቦች በመራቅ ምድቡን በበላይነት ማጠናቀቁን አረጋግጧል።

ጋዲሳ መገርሳ

መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *