ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በጥቁር ባህር ላይ የሚያደርጉትን ጦርነት ለማቆም ስምምነት ከመፈጸሟ በፊት የተወሰኑ የምዕራባውያን ማዕቀቦች መነሳት አለባቸው ስትል ተናግራለች።
ሩሲያ የጥቁር ባሕር የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው የምግብ እና ማዳበሪያ ንግዷ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ሲነሱ መሆኑን አስታውቃለች።
አሜሪካ ሁለቱ ወገኖች በጥቁር ባህር ላይ በሚደረጉ ጥቃቶች ዙሪያ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸዉን ባስታወቀች በሰዓታት ውስጥ፣ ክሬምሊን ዉሳኔዉን የምቀበለዉ በበርካታ የሩሲያ ባንኮች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከተነሳ ብቻ ነው ብሏል።
የሩሲያ ጥያቄ በአገሪቱ የግብርና ባንክ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ እና የድርጅቶቹን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓት መዳረሻ ገደብ እንዲነሳ የሚለዉን ያካትታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሞስኮ በወደብ ከተማዋ ሚኮላይቭ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፤ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጥቃቱ ግልጽ ምልክት ነው ሩሲያ ሰላም አትፈልግም ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሰንፔር እንዳለዉ
መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
