በግምጃ ቤት ነጠላ ሂሳብ ላይ ያተኮረ የምክክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል።

“ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ለመንግስት የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ጠቀሜታ ” በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የመድረኩ አላማ የግምጃ ቤት ነጠላ ሂሳብ (TSA) እና ዘመናዊ የጥሬ ገንዘብ አያያዝ አሰራሮች ላይ ግንዛቤን መፍጠር ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካዮች የመንግስት የገንዘብ አያያዝ ላይ ግንዛቤዎችን እየሰጡም ይገኛሉ።

የግምጃ ቤት ነጠላ ሂሳብ አያያዝ በቂ ግንዛቤ መኖር የመንግስትን የፋይናንስ ቅልጥፍና ያሳድጋል የተባለ ሲሆን፤በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ላይም በጎ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ተገልጿል።

የውይይት መርሃግብሩ በገንዘብ ሚኒስቴር እና ኤፍ.ኤስ.ዲ ኢትዮጵያ በጋራ የተዘጋጀ ነዉ፡፡

ልኡል ወልዴ

መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *