የኒጀር መፈንቅለ መንግስት መሪ ቃለ መሃላ ፈጸሙ

የኒጀር ወታደራዊ ገዥ ለአምስት ዓመታት የሽግግር ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ጄኔራል አብዱራሃማኔ ቺያኒ ከ2023 ጀምሮ ሀገሪቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን የኒጀር ተመራጩን ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙምን ከስልጣን ማባረራቸው የሚታወስ ነው፡፡

ትላት ረዕቡ እለት ጀነራል ቺያኒ የምዕራብ አፍሪካዊቷን ሀገር ህገ መንግስት በተካው አዲስ ቻርተር መሰረት የፕሬዚዳንቱን ቢሮ ይዘዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር ሃይል ጄኔራልነት ማዕረግ አሳድገዋል፡፡ይህ ብቻ አይደለም በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲፈርሱ በፊርማቸው ትእዛዝ ሰተዋል፡፡

መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *