ትራምፕ ከፋፋይ እና ዘርን ያማከለ ርዕዮተዓለምን የሚያንጸባርቁ ቅርሶች ከሙዚየሞች እንዲወገዱ አዘዙ፡፡

ትራምፕ ተገቢ ያልሆነ አስተሳሰብን የሚያንጸባርቁ ቅርሶች ከከፍተኛ የአሜሪካ ሙዚየሞች እንዲወገዱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የትራምፕ አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሙዚየሞች ውስጥ ከፋፋይ እና ዘርን ያማከለ ርዕዮተ ዓለም መስፋፋቱን የሚጠቁሙ ቅርሶች መኖራቸዉን አስታዉቋል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፀረ-አሜሪካዊ ርዕዮተ ዓለም የሚያንጸባርቁ ቅርሶችን ከዓለም ትልቁ ሙዚየም ከስሚዝሶኒያን ተቋም የማስወገድ እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

እውነትን እና ጤናማነትን ወደ አሜሪካ ታሪክ መመለስ በሚል በፈረሙት አዲስ ትዕዛዛ መሰረት፤ ሙዚየሙን አነቃቂ እና የአሜሪካን የታላቅነት ምልክት በማድረግ ወደ ትክክለኛዉ ቦታ ለመመለስ ይሰራል ብለዋል፡፡

ለዉጦቹን የመቆጣጠር ሃላፊነትም ለምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ሰጥተዋል፡፡

የስሚዝሶኒያን ተቋም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከፋፋይ በሆነ የዘር ርዕዮተ ዓለም ተጽእኖ ስር ወድቋል ሲል የትራምፕ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይገልጻል፡፡

በተቋሙ ዉስጥ የሚገኙት የአሜሪካ የሥነ ጥበብ ሙዚየም እና የአፍሪካ አሜሪካዊያን ታሪክ እና ባህል ብሔራዊ ሙዚየም በትራምፕ ትዕዛዝ የአሜሪካን እና የምዕራባውያንን እሴቶች በተፈጥሯቸው ጎጂ እና ጨቋኝ አድርገው የሚያሳዩ ትረካዎችን የሚያስተዋውቁ ናቸዉ በሚል ከተጠቀሱት መካከል ናቸዉ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *