ደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ለመግባት በቋፍ ላይ እንደምትገኝ የተባበሩት መንግስታት ገለጸ

በቅርቡ በደቡብ ሱዳን መሪዎች መሃከል የተፈጠረው አለመግባባት ሃገሪቱን ወደ የእርስ በርስ ጦርነት ሊያስገባት ጫፍ ላይ መድረሱን የገለጸው የተባበሩት መንግስታት፤ ጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ ነው ብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪች፤የደቡብ ሱዳን መሪዎች ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር እልህ መጋባታቸውን ወደ ጎን ብለው ለሰላም በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ህዝብ የእርስ በርስ ጦርነት ይከሰታል በሚል በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ደቡብ ሱዳን በኢኮኖሚ መላሸቅ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በጦርነት ስጋት ምክንያት ወደ 9.3 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግስታት አስታዉቋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የሱዳን መሪዎች ከግል ስሜታቸው ይልቅ የህዝቡን ፍላጎት እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርቧል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

ገነነ ብርሃኑ

መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *