የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለፔን በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ማጭበርበር ክስ ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

የቀኝ አክራሪ ብሄራዊ ራሊ (አርኤን) የተሰኘዉ ፓርቲያቸዉን ለመደገፍ የአውሮፓን ገንዘብ አለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል ነዉ ጥፋተኛ የተባሉት፡፡

ዳኛው ቅጣቱ ምን እንደሚሆን እስካሁን አልገለጹም፡፡

ባለፈው አመት አቃቤ ህጎች ቅጣቱ 3መቶሺህዩሮ እና የእስር ቅጣት እንዲኖረዉ የጠየቁ ሲሆን፤ለአምስት አመታት ለህዝብ ሹመት ከመወዳደር መታገድ አለባቸዉም ብለዋል፡፡

ይህም በ2027 ለፈረንሳይ ፕሬዚዳንትነት የመወዳደር ተስፋቸዉን ያጨናግፈዋል ተብሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *