ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ የወጣውን ማሻሻያ አዋጅ በሁለት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የማሻሻያ አዋጁ በአተገባበር ወቅት የታዩ ክፍተቶችን ከመሙላትም ባሻገር ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል እና ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በተሻሻለው አዋጅ መሠረት የሚወሰደው እርምጃ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችልም ነው ብለዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ በበኩላቸው ማሻሻያ አዋጁ ህገ – መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበርም ሆነ የጊዚያዊ አስተዳደር የቆይታ ጊዜ ማራዘምን አስመልክቶ በምን ያህል ጊዜ እንደሚሻሻል ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት እና ተጨማሪ ስራዎችን ለመስራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
